ሀገሬ ቲቪ

ትልቁ የሱናሚ አደጋ

በፈረንጆች የገና በአል ማግስት በደቡብ ምስራቅ እስያ ከህንድ ውቅያኖስ የተለመደው የባህር ዳር መዝናኛዎች ደምቀዋል ፣ ቱሪስቶች በተለያዩ በኢንዶንዢያ ባህር ዳርቻወች ይዘናናሉ ። ቀኑ እንደተለመደው ይመስል ነበር ።

ኢንዶኔዥያ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ አከባቢ የተለመደ የሚመሰስል የወሃ ሞግድ የመስል እንቃስቃሴ ይታይ ነበር ። ነገሩ ግን እንደታሰበው አልነበረም።

ክስተቱ ከ9.1 እስከ 9.3 ሪክተር ስኬል የሚለካ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ ። የዚህ መሬት መንቀጥቀጥ ደግሞ ወደ 100 ሜትር ከፍታ ያለው ኃይለኛ ሱናሚ በሕንድ ውቅያኖስ በማስነሳት በባህሩ ዳርቻ የሚገኙ የማህበረስብ ክፍሎችን ውጦ አስቀረ ።

ይህም ክስተት በታሪክ ከተመዘገቡት እጅግ አስከፊ ከሆኑት የተፈጥሮ አደጋዎች በአንዱ ሆነ ። ይህ አደጋ በአጠቃላይ 14 ሃገራትን ጎድቷል ።

አደጋው ክፉኛ ከጎዳቸው ሃገራት መሃከል ደሞ ኢንዶኔዥ ፣ ስሪ ላንካ፣ ሕንድ እና ፣ታይላንድ በዋናነት ይጠቀሳሉ ። አደጋው በአጠቃላይ ከ230 ሺ በላይ ዜጎችን ህይወትን ያሳጣ ነበር።

ከአጠቃላይ ሟችቾች ወስጥ ኤንዶንዢያ ከ170ሺ በላይ ዜጎቿን በሞት ተነጥቃለች ።ሲርላንካ በበኩሏ ከ 35 ሺ በላይ ዜጎቿን አጥታበታለች።

የሱናሚ አደጋው በእሲያ በቻ ተወስኖ አልቀረም ከ5ሺ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዞ ጎረቤት ሃገር ሶማሊያም ከ200 በላይ ዜጎችን ለሞት ዳርጓል ።

አደጋው ከሰው ሞት ባሻገር በኢኮኖሚውም ረገድ በባህር ዳርቻው የሚገኙ የቱሪዘም ሎጆችን እና የአሳ ገበያዎችን እንዲሁም ከተሞችን ከእንቅሰቃሴ ውጪ እንዲሆኑም አድርጓል ።

የሱናሚው አደጋ እንዲከሰት እንደምክንያት የተጠቀሰው የመሬት መንቀጠቀጥ በምድር ከታዩ የመሬት መንቀጠቀጦች በ3ተኝ ደረጃ የሚመመደብ ነው ።

በአደጋው የተጎዱ የ 14 ሃገራት ዜጎችን ለመደገፍ የአለም ሃገራት ተባብረው ከ 14 ቢሊየን ዶላር የሚበልጥ ድጋፍን አደርገዋል ።

ይህ ክስተት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከተከሰቱ አጠቃላይ አደጋዎች ትልቁ እና አስፈሪ ክስተት ነው ።በህንድ ውቂያኖስ የሚከስተው ሱናሚ ዛሬም ድረስ ቀጥሉ ለቀጠናው ፈተናው እንደሆነ ይገኛል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-26