ኢትዮጵያ የኮሌራ በሽታን እስከ 2028 ድረስ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር እንዲሁም በኮሌራ በሽታ ሳቢያ የሚከሰተውን የሞት ምጣኔ በ90 በመቶ ለመቀነስ የሚያስችል ፕሮግራም በይፋ ተጀምራል።
ፕሮግራሙን 4.4 ሚሊየን ዶላር በጀት ሲያዝለት 16 ሚሊየንን ሰዎች በፕሮግራሙ ተደራሽ ይሆናሉ ተብሏል።
በኢትዮጵያ በየጊዜው በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ እና ሰዎችን ለከፋ ጉዳት ብሎም እስከ ሞት ከሚያደርሱ በሽታዎች መካከል አንዱ የኮሌራ በሽታ ነው።
ይህንን በሽታ እስከ 2028 ለመቆጣጠር የሚያስችል ፕሮግራም አስጀምራለች። በፕሮግራሙም በተደጋጋሚ ወረርሽኙ የሚከሰትባቸው ቦታዎች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።
የኮሌራ በሽታ በንፅህና ጉድለት የሚመጣ ነው ያሉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስተር ኢንጂነውር ሃብታሙ ሚኒስተር መስራቤታቸው ይሄንን ችግር ለመቀነስ ከጤና ሚኒስተር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ፕግራሙ በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ ለመስራት ዝግጅት ይደረጋል። ለዚህም ደግሞ 4.4ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦለታል።
በማህሌት አማረ
2022-12-26
