ቤናዚር ቡቶ ፓኪስታንን ለመምራት ከህዝቡ ቅቡልነት አጊንታ የተመረጠች የመጀመሪያዋ ሴት ነች።
በቀደሙት ዓመታት በሴት ጠቅላይ ሚኒስተር ተመርተው የማያውቁት የሀገሬው ዜጎች እንስቷን ዙፋኑ ላይ በማየታቸው ግማሹ ሲደሰቱ አንዳዶች ደግሞ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።
ታዲያ ሁለት ጊዜ በፓኪስታን ዜጎች ተመርጣ ሀገሯን በማገልገል ላይ የነበረችው ይቺ ሴት በአንድ መድረክ ላይ ንግግር እያረገች ሳለ በተተኮሰባት ጥይት ተመታ የተገደለችው በዛሬዋ ዕለት 2007 ዓ.ም ነበር ።
ቤናዚር ቡቶ በፓኪስታን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስተር የዙልፊካር አሊ ሴት ልጅ ስትሆን አባቷ በተቃዋሚዮች ከተገደሉ በኋላ የ ሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ለመሆን ።
በወቅቱ የመሪነት ቦታውን መረከቧ በበርካቶች ዘንድ ተቃውሞ አስነስቷል። በተለይም እሷ ሙስሊም ሀገርን የመምራት አቅሙ የላትም የሚሉ ሀይሎች መበራከታቸው የስልጣን ዘመኗን ፈትነውታል ።
በሂደት የሷ ደጋፊ የሆኑ ግለሰቦችን ማፍራት የቻለችው ቤናንዚ ቡቶ ሁለት ጊዜ ተመርጣ ሀገሯን የመራችበት የጊዜ ገደብ በማለቁ በታህሳስ ወር የሀገሪቱ ዜጎች ለ 3ኛ ጊዜ እንዲመርትጧት ቅስቀሳ ማድረግ ትጀምራለች።
ተቀናቃኝ ሀይሎችም በፊናቸው እሷን ከመሪነት ለማውረድ እንቅስቃሴ ጀምረዋል ።
እ.ኤ.አ ታኅሣሥ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ልክ በዛሬዋ ቀን ቡቶ በአንድ መድረክ የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ሳለች ባልታሰበ ሁኔታ ቢላል በተባለ የ15 ዓመት ታዳጊ በተተኮሰ ጥይት ተመታ ወደቀች።
ታዳጊውም ኢላማው ጠቅላይ ሚኒስትሯ ላይ ማረፉን እንዳረጋገጠ ራሱ ላይ ተኮሰ። የጠቅላይ ሚኒስትሯ የግድያ ዜና እንደተሰማም በፓኪስታን ከፍተኛ የእርስ በርስ ብጥብጥ ነገሰ ።
ደጋፊዎቿ መንገዶችን በመዝጋት ፣ እሳት በማንደድና መፈክሮችን በማሰማት ሀገሪቱን ውጥረት ውስጥ ከተቷት ። በወቅቱም ከ 20 በላይ ሰወች ሞተዋል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-12-27
