ሀገሬ ቲቪ

ከነገ ጀምሮ ወደ መቀሌ መደበኛ በረራ እንደሚጀመር ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን ከአዲስ አበባ መቀሌ የአየር ትራንስፖርት በነገው ዕለት እንደሚጀምር አስታወቀ።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የአቬየሽን ሰራተኞች ወደ መቀሌ አቅንተው አየር መንገዱ ለበረራ ምቹ መሆኑን አረጋግጠዋል ብለዋል ።

ነገ የሚጀምረው በረራ በቀን አንድ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን የደንበኞቹን ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የበረራው ቁጥሩ ከፍ ሊል ዋና ስራ አሰፈጻሚው ገለጸዋል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-12-27