በዓለም ባንክ ድጋፍ በተተገበረው የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ከ20 ሺሕ በላይ በጎዳና ላይ የነበሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በፕሮግራሙ 20,991 ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ህጻናት፣ አዋቂዎች፣ ህጻናትን ያያዙ እናቶች እና አረጋዊያን ተጠቃሚ ሆነዋል ነው የተባለው።
የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት በሀገራችን ባሉ 11 ከተሞች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-12-27
