ሀገሬ ቲቪ

ዩክሬን የሰላም ጉባኤ ማድረግ እንደምትፈልግ ገለፀች

የሩሲያ እና የዩኩሬን ጦርነት እንዲያበቃ በሁለት ወር ውስጥ የመሪዎች የሰላም ጉባኤ ማካሄድ እንደምትፈልግ የዩኩሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ድሚትሮ ኩሌባ ገልፀዋል።

ዩኩሬን ሰላም ነው የምትፈልገው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ በሰላም ጉባኤው ላይ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንዲሳተፉ ሃገራቸው እንደምትፈልግ ገልፀዋል።

ሩሲያ በሰላም ጉባኤው ላይ ትሳተፋለች የሚል እምነት እንደሌላቸው መናገራቸውን አሶሴትድ ፕረስ ዘግቧል።

በማህሌት አማረ
2022-12-27