ሀገሬ ቲቪ

የሰላም ስምምነቱ የአፍሪካ ህብረት የአደራዳሪነት አቅም ከፍ ማለቱን ማሳያ ነው ተባለ

በኢትዮጲያ መንግስት እና በህወሀት መካከል የተደርሰው የሰላም ስምምነት የአፍሪካ ሃገራት ለችግሮቻቸው አፍሪካዊ መፍትሄ እንዳላቸው ማሳያ ነው ተባለ ።

የሰላም ስምምነቱ መደረሱ እና ወደ ተግባራዊ እርምጃ መወሰዱም የአፍሪካ ህብረት የማደራርደር አቅሙ እየጨመረ መምጣቱን አመላካች ነው ተብሏል ።

ሀገራት እና መሪዎች በአፍሪካ ቀጠና ለሚከስቱ ግጭቶች በሰላማዊ ውይይት እና ድርድር ለመፍታት እያሳዩ የሚገኙት ቁርጠኝነት በአፍሪካ በግጭቶች ዙሪያ የመነጋገር ፖለቲካ እያደገ መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው ተብሏል ።

የአፍሪካ ህብረት ግጭቶችን ለመፍታት ከውይይት እና ከድርድር ባሻገር ባህላዊ የ እርቅ ስነ_ስርዐታቶችን መጠቀም እንደሚገባም ተጠቁሟል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-28