ሀገሬ ቲቪ

ሁሉም አካባቢዎች አፋጣኝ የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ እንደሚገባ ተገለፀ

ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን በኢትዮጲያ በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች አፋጣኝ የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ይገባል አለ ።

በአፋር፣ በአማራ፣ በትግራይ እንዲሁም በደቡብ ክልል የሚገኙ ህዝቦች በጦርነት እና ድርቅ ሳቢያ አስከፊ ጊዜያትን እያሳለፉ እንደሆነ ቡድኑ ገልጿል። ከ22 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አፋጣኝ ሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል ።

በሶማሌ ክልል ከአርባ አመታት ውስጥ የከፋ የሚባል ድርቅ ተከስቷል ፤ በጋንቤላ ክልልም የጎርፍ አደጋ ከ180 ሺ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል ሲል ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድኑ መግለፁን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።እነዚህ ሁሉ አፍጣኝ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋልብሏል።

በማህሌት አማረ
2022-12-28