በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራአስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይፋ አደረጉ።
በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የስልክአገልግሎት በዛሬው ዕለት መቐለ ላይ የተሳካ ጥሪ ማድረግ መቻሉን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም 981 ኪሎ ሜትር የፋይበር ጥገና ተከናውኖ በ 27 ከተሞች የስልክና ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ማስጀመር ተችሏል ብለዋል።
የቴሌኮም አገልግሎቱ ዳግም መጀመር በመቻሉ 61የባንክ ቅርንጫፎችም ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ እንደተቻለ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ከአዲስ አበባ መቀሌ ዳግም በረራ መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቋል፡፡ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ መቀሌ የአየር ትራንስፖርት ዛሬ ቀን 6 ሰዓት ላይ በይፋ ተጀምሯል ።
የአየር ትራንስፖርቱ በሁሉም የትግራይ ክልል መዳረሻዎች ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡
በዮሴፍ ከበደ
2022-12-28
