ሀገሬ ቲቪ

የቀድሞ የአንጎላ ፕሬዝዳንት ሴት ልጅ ንብረት እንዲወረስ ታዘዘ

የቀድሞ የአንጎላ ፕሬዝዳንት ኤዱዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ሴት ልጅ የሆነችው ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ ንብረቷ እንዲወረስ ታዘዘ።

ትዕዛዙን ያስተላለፈው የአንጎላ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሆነ አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ በሀገሪቱ ከ1 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ጉዳት በማድረሷ ይህ ውሳኔ ሊተላለፍ ችሏል ብሏል ።

ግለሰቧ በሙስናና በሌሎች ወንጀሎች በመሳተፍ ያፈራቸው ሀብት መሆኑም ታውቋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-12-28