ደቡብ ኮሪያ ድንበሯን የጣሱ አምስት የሰሜን ኮሪያ ድሮኖችን መምታት አለመቻሏን ተከትሎ ዜጎቿ ስጋት አድሮባቸዋል ተባለ።
የሀገሪቱ የመከላከያ ኃይል የሰሜን ኮሪያ ድሮኖቹን መምታት ላለመቻሉ ይቅርታ ጠይቋል። ድርጊቱ ብዙ የደቡብ ኮሪያ ዜጎች ላይ ስጋት አሳድሮባቸዋል።
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮል ድርጊቱ የመከላከያ ኃይላችንን የልምምድ ማነስን ያሳያል ብለዋል።
የሰሜን ኮሪያ ድሮኖች በደቡብ ኮሪያ የአየር ክልል እንደልብ ሲመላለሱ ወለው አንድም ጥቃት ሳይደርስባቸው መመላለሳቸው ነው ስጋት ያሳደረው።
በአብርሃም በለጠ
2022-12-28
