የአውሮፓ ኅብረት ከአፍሪካ ሀገራት የሚገቡትን የተፈጥሮ ጋዝ በማሳደግ ከሩሲያ ጥገኝነት ለመላቀቅ አቅዷል ተባለ። ብሉምበርግ የተሰኘው የዜና ምንጭ ተመለከትኩት ባለው ሰነድ የአውሮፓ ኅብረት ከሩስያ የሚግባውን የተፈጥሮ ጋዝ በዚህ ዓመት ሁለት ሶስተኛውን ለመቀነስ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንዳቀደ አስታውቋል። በአፍሪካ በተለይም በአህጉሪቱ ምዕራባዊ ክፍል እንደ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና አንጎላ ያሉ ሀገራት በአብዛኛው ያልተነካ የተፈጥሮ ጋዝ የተካማቸባቸው ሀገራት ተብለው በሰነዱ ላይ መስፈራቸውን የዜና ምንጩ ገልጿል። ምዕራባውያን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ሲሉ የሚገልጹትን ድርጊት ፈጽማለች በማለታቸው ነው ይህን ዕቅድ የነደፉት የአውሮፓ ኅብረት ረቂቅ ሰነድ እንደሚያመለክተው የአውሮፓ ኅብረት ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝን በ 50 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ለመጨመር አቅዷል።
በሀገሬ ቲቪ
2022-05-03
