የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኬሚካል እና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከልን የ2013 ዓ.ም. የበጀት ዓመት የሂሳብ ህጋዊነት ኦዲት ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል።
በፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በቀረበለት ሪፖርት ላይ የማስተካከያ ስራዎችን መስራት የነበረበት ማዕከሉ የቀረቡለትን የፋይናንስ ክፍተቶች ላይ ማስተካከያዎችን እያደረገ አለመሆኑ በቋሚ ኮሚቴው አባላት ተነስቷል።
ማዕከሉ ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ካለጨረታ ግዢ ምፈፀም፣ ከ8.9 ሚሊዮን በላይ የሚያውጣ አገልግሎትን ካለጨረታ ከአንድ አቅራቢ ብቻ ማግኘትን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ከግዢ ጋር የተያያዙ ክፍተቶች እንዳሉበት በሪፖርቱ ተጠቁሟ።
በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሰጡት የማዕከሉ የስራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ተከታዩን ብለዋል።
በማዕከሉ ውስጥ የተገኙ ክፍተቶችን በተመለከት ምላሽ የሰጡት የኢንዱስትሪ ሞንስትሩ አቶ መላኩ አለ በል ክፍተቶቹ መገኘታቸውን አምነው ሚንስቴር መስሪያቤታቸው የእርምት እርምጃዎችን እንደሚወስድ ጠቁመዋል።
የ2010 በጀት ዓመት ያልተስተካከለ የሒሳብ ሪፖርት ያለበት ተቋሙ በቀጣይ የቀረቡበትን ክፍተቶች ለማረም የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ታህሳስ 30 ለቋሚ ኮሚቴው እንዲያሳውቅ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-12-28
