ኮቪድ 19 ለመጀመሪያ ጊዜ የታየባት ሀገር ናት የምትባለው ቻይና ቫይረሱ እንደሌሎቹ ሀገራት ጠንከር ያለ ጉዳት ሳያስከትልባት ልትከላከለው ችላ ነበር። ከቅርብ ቀናት በኋላ ግን ሁኔታዎች የተለዋወጡ ይመስላሉ።
ቫይረሱ ከቁጥጥር ውጪ በመውጣት የሥርጭት አድማሱን አስፍቷል። በዚህም ምክንያት በሀገሪቱ የማስታገሻ መድኃኒት ዕጥረት ተክስቶ ዜጎች ችግር ውስጥ መግባታቸው ተሰምቷል።
በመድኃኒት ቤቶች የሚታይ ግርግር እና ትርምስ በርትርቷል። ማስታገሻ መድኃኒት ለማግኘት እንደ ገመድ በረዛዘሙ ሰልፎች ላይ ሰዎች ተስፋ ሳይቆርጡ ከኋላ በመሰለፍ መድኃኒቱን ለመግዛት ሲጥሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ሳውዝ ቻይና ሞርኒግ ፖስት የተባለው የዜና ምንጭ አሳይቷል።
በመድኃኒት መደብሮች ተስፋ የቆረጡት ደግሞ መድኃኒት ፋብሪካ በር ላይ መሰለፍን መርጠዋል። ምክንያቱ ደግሞ በትክክለኛው ዋጋ ለመግዛት በማሰብ ነው።
የተወሰኑ የጤና ተቋማት ደግሞ በውጪ በኩል የተወሰኑ መድኃኒቶችን በፕላስተር በራቸው ላይ ለጥፈው ጠንከር ያለ ትኩሳት ያጋጠመው አሊያም የጠናበት ሰው በነጻ እንዲወስድ እያደረጉ ነው።
በርካታ ሕመምተኞች ታዲያ ይህን ማስታገሻ መድኃኒት ለማግኘት አልቻሉም።
ለሕፃናት የሚሸጠው መድኃኒትም ዋጋው ጣራ መንካቱ ተሰምቷል በፊት ይሸጥበት ከነበረው ዋጋው 100 ዕጥፍ ተመንድጎ 3ሺህ የቻይና ዩሀን ወይም 430 ዶላር እየተሸጠ ነው።
በሙሉጌታ በላይ
2022-12-28
