የአፍሪካ ህብረት ልዮ መልእክተኛ የቀድሞው የናይጄርያ ፕሬዝደንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እንዲሁም ፤ የቀድሞ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸም ለመገምገም መቀሌ ገቡ።
የኢንግሊዝን ጨምሮ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት አምባሰደሮችም መቀሌ ደርሰዋል። ከአምባሳደሮቹ ጋር የፍትህ ሚንስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ተገኝተዋል።
በመቀሌ ቆይታቸውም በሰላም ስምምነቱ አፍጻጸም ዙርያ ከትግራይ መንግስት እና ከፌደራል መንግስት አመራሮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በብሩክ ያሬድ
2022-12-29
