በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ሳቢያ በአካባቢው ያሉ ቅርሶች ያሉበት ሁኔታ ሊጠና ነው ተባለ።
የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ ቀደም የቅርሶቹን ሁኔታ ለመገምገም ያዋቀረው ቡድን ወደ ስራ ሊገባ መሆኑን አስታውቋል።
ቡድኑ በአካባቢዎቹ ያሉ ቅርሶች በጦርነቱ ምን ያክል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና አሁን ላይ ያሉበት ሁኔታን አጣርቶ እንደሚያሳውቅ የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ነዳች ጀማል ተናግረዋል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-12-29
