የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ግጭት በነበረባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ነዳጅ የሚያከፋፍሉ 14 ኩባንያዎች ፤ በቀጥታ ከጅቡቲ እንዲጭኑ ፈቃድ መሰጠቱን አስታወቀ።
በባለስልጣኑ የነዳጅ አቅርቦት ሎጅስቲክስና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ሹመት ነዳጅ እንዲጭኑ የተፈቀደላቸው 14 ኩባንያዎች ፤ በሰሜኑ ክፍል ግጭት ከመከሰቱ በፊት በዛ አካባቢ ይሠሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል፡፡
በግጭቱ ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት ተቋረጠባቸው በነበሩ አካባቢዎች ያለውን ነዋሪ በፍጥነት ተጠቃሚ ለማድረግ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-29
