
ደቡብ ሱዳን ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ በምትዋሰንበት ምስራቃዊ ድንበር ዙሪያ 750 ወታደሮች ማስፈሯን ይፋ አደረገች።
በቅርብ ወራት ውስጥ የዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ወታደሮች ኤም 23 ከሚባለው አማፂ ቡድን ጋር ውጊያ እያደረጉ ይገኛሉ።
ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ትልቅ የተባለውን የጋራ ጥምር ጦር በደቡብ ሱዳን ድንበር አስፍረዋል።
ከኬኒያ ብሩንዲ እና ዩጋንዳ ለተውጣጡት ወታደሮች ሽኝት ያደርጉት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ፤ ጥምር ጦሩ የሀገሪቱን ድንበር እና የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ አደራ ብለዋል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-12-29