አሜሪካ ከቻይና ወደ ሀገሯ የሚገቡ ተጓዞች ከኮቪድ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምርመራ ውጤት ማምጣት አለባቸው አለች ።
ሲኤንኤን እንደዘገበው ተጓዞቹ ከቻይና ከመነሳታቸው ሁለት ቀናት በፊት ተመርምረው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ ግድ ይላቸዋል ። ይህን ሳያደርጉ ወደ አውሮፕላን መሳፈር እንደማይችሉም ነው የተገለጸው።
ይህ ውስኔ የተላለፈው በቻይና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በድጋሜ የስርጭት አድማሱ መስፋቱን ተከትሎ ነው።
ምን ያህል የስርጭት አድማሱ ሰፍቷል የሚለው እንዳይታወቅ ቻይና ለመረጃ ግልጽ አለመሆኗ ፤ ጉዳዩን አዳጋች እንዳደረገው የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-12-29
