የተፈጥሮ የሰው ፀጉር ወይንም ሂውማን ሄር ለበርካቶች የመነጋገሪያ አጀንዳ ነው።
እነዚህ ተፈጥሮን ፀጉር አይነቶች ለሴቶች የውበት መጨመሪያ አልያም ውበትን ማጉያ ተደርገውም ጭምር ይወሰዳሉ።
ታዲያ አሁን እነዚህ ፀጉሮች የማስዋብ አገልግሎታቸው ሲያበቃ ከመታል እና አካባቢን ከመበከል ተርፈዋል መባሉን ሰምተናል።
ለነገሩ አገልግሎታቸውን የጨረሱ ተፈጥሯዊ የፀጉር መዋቢያዎች ብቻ ሳይሆኑ በየፀጉር ቤቱ ከሰዎች አናት ላይ የሚቀነሱ ፀጉሮችም ለዚሁ አገልግሎት እየዋሉ ይገናሉ።
በቤልጀም ያሉ የፀጉር ቤቶች የደንበኞቻቸውን ፀጉር ከመቁረጥ ባለፈ የወዳደቀ ፀጉር ሰብስበው በከረጢት ሞልተው ያዘጋጃሉ።
ፀጉሮችን መልሰው ወደ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ፕሮጀክት ሀገር በቀል በሆነ የተራድዖ ድርጅት የሚከወን ነው።
ከየቦታው የተሰበሰበው ፀጉር 60 ሳንቲ ሜትር 60 ሳንቲሜትር በሆነ ስፋት ምንጣፍ መሰል የፀጉር ስጋጃ እንዲሆን ተደርጎ ይዘጋጃል።
ታዲያ ይህ የፀጉር ስጋጃ አካባቢን ለመበከል ከፍተና ሚና ያላቸውን እንደ ቅባት፣ ዘይት፣ እና የተፈጥሮ ነዳጅን ከውሃ ውስጥ በቀላሉ ለመለየት የሚረዳ ነው።
የፕሮግራሙ ተባባሪ መስራች ይህንን ይላሉ።
እኛ 60 በ60 በሆነ መጠን የምናዘጋጃቸው የፀጉር ስጋጃዎች በሦስት ደረጃዎች የሚዘጋጁ ናቸው። ይህንን ለማዘጋጀት አንድ ኪሎግራም ፀጉርን እንጠቀማለን። ይህ አንዱ ስጋጃ ከሰባት እስከ ስምንት ሊትር የሚሆን ሃይድሮ ካርበን፣ ዘይት እና የነዳጅ ዘይትን ተፈጥሮን እንዳይበክል መጦ መታዝ ይችላል።
ይህ የፀጉር ስጋጃ በሀገር ውስጥ መመረቱ የበለጠ ጥቅም እየሰጠ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል።
በተለይ በዓለም ላይ ያሉ ከምናኝከው ማስቲካ ጀምሮ ሁሉም ነገሮች ለመሰራታቸው የፔትሮሊየም ምርትን ይጠቀማሉ።
ይህ ስጋጃ ከሰዎች የተፈጥሮ ፀጉር በተፈጥሯዊ መንገድ ብቻ የሚዘጋጅ ነው።
እንደ ተታታሪ መስራቹ ከሆነ ይህ ተፈጥሮን ለማከም ይውላል የተባለው ስጋጃ ከውጭ ወደ ቤልጄም የሚገባ አይደለም።
ምርቱ በሀገር ውስጥ ተመርቶ የሀገሪቷን የተፈጥሮ መበከል ለማከም አገልግሎት እንዲሰት እየተደረገ ይገኛል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-12-29
