የተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በድምቀት የሚያከብሩት የገና በዓል በደረሰ ቁጥር የተለያዩ አስገራሚ የበዓል አከባበሮችን እንመለከታለውን ። ላይ ካሉ አስደናቂ የገና በዓል አከባበሮች መካከል አንዱን እንንገራቹ።
ከወደ ፔሩ ነው። እንደ አብዛኛው የ አለማችን ክፍሎች ያላቸውን ሁሉ በማድረግ የገና በዓልን በድምቀት ያከብራሉ።
ታዲያ ከመብላት ከመጠጣት እና ከመደሰት ባለፈ ፔሩዎች የገና በዐል ሲደርስ ታናኩይ የሚባል ውድድር ያዘጋጃሉ። በክብ በታጠረ ገመድ ውስጥ በመግባት ቡጢ መሰናዘር።
የቡጢ ወይም የቦክስ ውድድር ብዙ ቦታ የተለመደ ነውና ምን ያስገርማል ካላችሁን ደግሞ ውድድሩ የሚደረገው አመቱን ሙሉ በተቀያየሙ ሰወች መካከል ነው እንሎታለን። ነገሩ እንዲ ነው መቼም ሰው ነንና በአንዳንድ ነገሮች መጋጨት እና መቀያየም አይቀሬ ነው ።
ታዲያ በ ፔሩ ማህበረሰብ ህግ እንደተቅያየሙ እና እንደተኮራረፉ አዲስ አመትን መቀበል በጥብቅ የተወገዘ ነውና ቅያሜያቸውን እርግፍ አርገው ሚጥሉበት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህል አላቸው ይህም ሁለት የተቀያየሙ ሰወችን በገመድ የታጠረ መድረክ ላይ በማውጣት ማፋለም ። ነገሩ ይለይላቹ ነው።
ከሁለቱም ወገን ለሚሰነዝሩት ቡጢ ርህራሄ የለም፤ መምታት የሚቻልና የማይቻል ቦታ ህግ በሌለበት መድረክ ካሻው በ እግር ከፈለገም በእጅ የቻሉትን ሀይል ተጠቅሞ ጠላት ላይ ማሳረፍ።
የሁለቱ ተፍላሚ ደጋፊዎች ከሪንጉ ውጪ ሆነው በለው በለው በማለት ሞራል ይሰጣሉ። ተወዳዳሪዎችም ውስጣቸው ያለውን ቂም በማሰብ ጥርሳቸውን ነክሰው ይፋለማሉ።
ከውድድሩ ማብቂያ በኋላም ለአሸናፊው ተገቢውን ክብር በመስጠት ሁለቱም ቅያሜያቸውን እንዳነሱ አሳውቀው እርቅ ይፈጽማሉ ።
ይህ ባህል ወንዶችን ብቻ በማሳተፍ ረጅም ግዜያትን ያስቆጠረ ሲሆን ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ግን ሴቶችም ጥልን በቡጢ የመፍታቱን መንገድ መከተል ጀምረዋል።
ሀገራችንን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎች ጥልን የሚፈቱበት ባህላዊ የእርቅ ስርዐቶች ቢኖሩን የፔሩ የእርቅ መፍጠሪያ መንገድ ግን ብዙዎችን እያስገረመ በየአመቱ መከናወኑን ቀጥሏል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-12-30
