በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች 8.3 ሚሊዮን ህዝብ የዕለት ደራሽ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሺን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሺነር ዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያም ጉዳቱ በደረሰባቸው በሶስቱም ክልሎች የዕለት ደራሽ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች መለየታቸውን ጠቁመዋል።
የኤሌክትሪክ እና ማህበራዊ አገልግሎት በተለይም የጤና ተቋማት ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ በአካባቢዎቹ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዕለት ደራሽ ድጋፍ 141 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ ዕርዳታ ተደራሽ ሆኗል ብለዋል።
ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማሪያም የአጋር ድርጅቶች ድጋፍ የማድረግ ጥሩ ፍላጎት እያሳዩ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የነዳጅ አቅርቦት እና የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ለአካባቢዎቹ እንዲደርስም እየተደረገ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በግጭቱ ሲሳተፉ የነበሩ የሰራዊት አባላትንም መልሶ የማቋቋም ስራ ዝግጅት መጀመሩ ተገልጿል።
በአብርሃም በለጠ
2022-12-30
