የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት ለፈረሙት ዘላቂ የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበር አፍሪካ ኅብረት ያቋቋመው የመከታተያ፣ መቆጣጠሪያና ማረጋገጫ ሥርዓትን የሚመራ ሦስት አባላት ያሉት ቡድን መዋቀሩን ተገለጸ።
የስምምነቱ የመከታተያና መቆጣጠሪያ ሥርዓት የሚመሩት አባላት፣ የኬንያው ሜጀር ጀኔራል ራዲና ስቲፈን፣ የናይጀሪያው ኮሎኔል ኡመር ማይራጋ እና የደቡብ አፍሪካው ኮሎኔል ቴፎ ሰኮል እንደሆኑ ተገልጧል።
ቡድኑ ፌደራል ፖሊስ ትናንት በመቀሌ የፌደራል ተቋማትንና መሠረተ ልማቶችን ከሕወሃት ታጣቂዎች ሲረከብ ተከታትሏል ተብሏል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-12-30
