በትግራይ ክልል የሚገኘው መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በቅርብ ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጸ።
ፋብሪካው ከሰሜኑ ጦርነት ጋር ተያይዞ ሥራ ማቆሙ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በማዕድን ሚኒስቴር አማካኝነት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኝ መደረጉን የሲሚንቶ አምራቾች ማህበር ገልጿል፡፡
ሰራ ለመጀመር የሚያስችሉ በጣም አስፈላጊ የሆኑ መለዋወጫዎችን በአየር ትራንስፖርት እንዲደርስ በማድረግ በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል።
የፋብሪካው ወደ ሥራ መግባት በተለይም በአፋር፣ ጎንደር፣ ወሎና ትግራይ ያለውን የሲሚንቶ ምርት ፍላጎት ይሸፍናል ተብሏል።
በብሩክ ያሬድ
2022-12-30
