ሀገሬ ቲቪ

ለገና በዓል የፍጆታ እና የግብርና ምርቶች ላይ የተደረገው ዝግጅት

መጪው የገና በዓል የግብርና፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እና እንደ ዘይት እና ስኳር ያሉ ሸቀጦች ላይ እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትሥስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን፣ከኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና ከኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የመጡ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች እና ስለዋጋቸው የኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ አብዲ ዑመድ ገለጻ አድርገዋል።

በዓሉ ቅዳሜ በመኾኑ የእሁድ ገበያው አርብ ላይ የሚጀመር መኾኑን ተናግረው፤ ከ 161 ሺህ ኩንታል በላይ የግብርና ምርቶች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ሸማች ማኅበራት ከዶሮ እስከ በሬ ያሉ የእርድ እንሣት እና የእንሣ ተዋጻኦ ያቀርባሉም ብለዋል።

100ሺ እስከ 150 ሺ ኩንታል ስኳር ለበዓል እንደሚሰራጭ እና የተከሰተውን እጥረት ለማረጋጋት ዝግጅት መደረጉን በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የማርኬቲንግ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታፈሰ አሰፋ ተናግረዋል።

ሌላው በዘይት ምርት ላይ ስለተደረገው ዝግጅት መግለጫ የሰጡት የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ም/ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቀጸላ ሸዋ ረጋ መንግሥት 43 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መኾኑን ገልጸው ለበዓሉ ከተመደበው 30.3 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለአዲስ አበባ 5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ተመድቧል ብለዋል።

በንግድ ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መስከረም ባህሩ ለክልሎች በሚከፋፈለው ዘይት ውስጥ ለትግራይ ክልል ከ 1 ሚሊዮን በላይ ሊትር ዘይት መመደቡን አስታውቀዋል።

የስኳር የፋብሪካ በር ዋጋ በኪሎግራም 57 ብር ነው ተብሏል። ዘይት 3ሊትር 314፣5 ሊትር509 ብር እና 20 ሊትር 2001 ብር ይሸጣል ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-02