ሀገሬ ቲቪ

ለእናቶች ሞት ምክንያት እየሆነ የሚገኘው በሽታ ኢክላምሲያ

ኢትዮጲያ የእናቶች ሞት ለመቀነሰ የተቀመጠውን አለም አቀፍ ግብ አሰቀምጣ እየሰራች ትገኛለች።እስካሁን ባለ መረጃ ከመቶ ሺ እናቶች 676ቱ ከወሊድ ጋር በተያያዘ በሚፈጠሩ የጤና እክሎች ይሞታሉ ።

ለዚህ ምክንያት ከሆኑ ህመሞች በእርግዘና ወቅት የሚከሰተው የደም ግፊት ወይንም ኢክላምሲያ አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጲያ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ኢክላምሲያ በሽታ በእናቶች ላይ በእርግዝና ወቅት ከ 5 ወር ጀምሮ የሚከሰት ሲሆን አንዳንድ ግዜ በምጥ ሰአትም ሊከስተ የሚችል በሽታ ነው ። በሽታው በፍጥነት ህክምና ካላገኘ እናት እና ልጅን ህይወት ሊቀጥፍ ይችላል ።

በሽታው በምልክት ደረጃ ይህ ነው የሚባል ምልክት ማሳየት ባይችልም ከፍተኛ የእራስ ምታት ፣ ተንፋሽ ማሳጠር እና የደም ግፊት መጠኑ ከመጠን ካለፈ እራስን ማሳት ምልክቶቹ ናቸው ።

ይህን ጉዳት በእናቶች ላይ ያስተከትል እንጂ በጽንሱ ላይም ከፍተኛ ጉዳትን እንድሚያስከትል የማህጸን እና ጸንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር ፈላጎት ታደሰ ተናግረዋል ።

የኢክላምሲያ ወይንም በእርግዘና ወቅት ከ5ወር ጀምሮ የሚከሰውተው የደም ግፊት በሽታ ጉዳት ሳይደርስ ለመከላከል ተከታታይ የሆነ የጤና ክትትል ያሰፈልጋል ተበሏል።

በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-02