እስካሁን ባልተቋጨው የሩሲያ እና የዩኩሬን ጦርነት ሳቢያ ሩሲያ በጦርነቱ ላይ ያላትን እቅድ አውሮፓዊያኑ አለማወቃቸው ስጋት ፈጥሮባቸዋል፡፡
ጦርነቱ እንዲያበቃ መልካም ፍቃዷ እንደሆነ ስትገልፅ የቆየችው ሞስኮም ኪየቭን በመደብደብ የፈረንጆቹን 2023 ተቀብላለች፡፡
ሩስያ በብዙ ቢሊዮን ዶላሮች ዘመናዊ የመከላከያ ኃይል ገንብታለች። በየጊዜው የጦር እስትራቴጂዎቿን፣ ቀይ መስመሮቿን መቀያየሯ ለምዕራባውያኑ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። 40 የሚሆኑ የጦር ድሮኖችን ወደ ኪየቭ መላኳ ተገልጿል።
በማህሌት አማረ
2023-01-02
