ጋና ነፃነትዋን እንደታገኝ የለፉ መሪ ናቸው ፣ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረትም ሚናቸው ቀላል የሚባል አይደለም የጋናው መሪ ኩዋሜ ኑኩሩማ ።
ጋና ነጻነቷን ከገኘች በኋላ በሃግሪቱ ሁለነትናዊ ለወጥ እንዲመጣ ሰርተዋል። ከዛሬ 58 አመት በፊት በዛሬው ቀን በግል በገዛ ጠባቂያቸው ካደረገባቸው የመግደል ሙከራ የተረፉበት ቀን ነው ። የ ዕለቱን ከታሪክ ትኩረታቸን ነው።
ጋና ነፃነትዋን ካገኘች ጀምሮም ለሀገሪቱ ቅኝ ግዛት ስርዓት በብርቱ ታግለዋል ፣ለጥቁር ህዝቦች አንድነትና ለፓን አፍሪካኒዝም ባለዉለታ ናቸው ኩዋሜ ኑኩሩማ።
ጋና ነጻንቱን ካገኘች በኋላ የመጀመሪያዉ የጋና ፕሬዝዳንት በመሆንም ሀገራቸውን አገልገለዋል ።ኑኩሩማን የሃገራቸው ዜጎችንም ቢሆን ለዓመታት ሲያስተዳደሩ የሀገሪቱን የቅኝ ግዛት ስነልቦናን ለመለወጥ እንዲሁም የሃገሪቷን ያላትን የተፈጠሮ ጸጋዎቿን እንድትጠቀም በዙ ጠረትን አደርገዋል ።
ሆስፒታል ፣ የባቡር አገለገሎት እና በሁሉ የጋና አከባቢዎች የትምህርት ተደራሽነት እንዲሰፋ ሰርተዋል ። ጋና ተከተለው በነበርውም የሶሻሊስት ርዕዮተ አለም ምክንያት እና ኩዋሜ ኑኩርማ ላህገራቸው ካበረክቱት አስተዋጸኦ አንጻር ከቀድሞ ሶቪየት ህብረት የሌኒን ሽልማት ተቀብለዋል ።
በወቅቱ የጋና የሰንደቅ አላማ ቀለም የጋናዊያን ሰነልቦና የሚወክል አይደለም በማለት በወቅቱ በአፍሪካ የነጽነት ትግል ወስጥ ሃገራት በአርማነት ይጠቀሙ የኢትዮጲያ ሰንደቅ አላማ የመሃሉን መደብ በመቀየረ ብቻ ዛሬም ድረሰ የሃገረቱ ባንዲራ እንዲሆን አድረገዋል ።
ከዚህም ባሻገር ኩዋሜ ኑኩሩማ በ4 የአፍሪካ መሪዎች አሳቤነት የተመሰረተው እና በጠቃላይ 32 የአፍሪካ ሀገራትን ይዞ ወደ ስራ የገባውን የቀደሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በቆርጥነት መስረተዋል።
ፕሬዝዳንት ኩዋሜ ንኩርማ በጋንዊያን ተወዳጅ መሪ ነበሩ ።በአንድ አጋጣሚ በዛሬው ቀን 58 አመት በፊት ፕሪዘዳንት ኩዋሜ ኑኩሩማን ያልታሰብ ነገር ገጠማቸው ከገዛ ጠባቂያቸው የመግደል ሙከራ ተደረገባቸው ።
በእንግሊዞች የሰለለጠነው ሳሊፉ ዳጋርቲ የተባለ የግል ጠባቂያቸው ለምሳ ከቢሮዋቸው ወጥተው ወደ መኪናቸው ሲያመሩ ይህ ጠባቂ ተኩስ ከፈተባቸው ኩዋሜ ኑኩሩማ ከአምስት ጥይቶች መሃከል ከሞት አፋፋ ተረፉ ። ፕሬዝዳንት ኩዋሜ ኑኩሩማ ላይ ተኩሰ የከፈተው ጠባቂም በዛው አጋጣሚ ተገደለ።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-02
