ሀገሬ ቲቪ

የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል እየወጡ መሆኑ ተጠቆመ

የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል እየወጡ መሆናቸውን መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።

የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል አልወጡም የሚለው ለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ትግበራ ተግዳሮት ተደርጎ በትግራይ ክልል መንግስትም ሆነ በውጭ ኃይሎች ሲነሳ ቆይቷል።

ከአካባቢው የሚወጡ የውጪና የሀገር ውስጥ መረጃዎች የኤርትራ ኃይሎች ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እየወጡ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም የሰላም ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር አቅም ይሆናል ተብሏል ።

በአብርሃም በለጠ
2023-01-02