ሀገሬ ቲቪ

የአቴከር ሕዝቦች መሪዎች ቃል መግባት

በኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ የሚኖሩና ተቀራራቢ ቋንቋን የሚጋሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ መሪዎች ሰላማዊ አብሮ መኖርን ለማጠናከር ቃል ገቡ።

መሪዎቹ በሀገራችን ኦሞ ዞን በተከናወነው የንያጋቶም ባህላዊ ሁነት ላይ ድንበር የሚጋሩት ማህበረሰቦች ሠላማዊ የሀብት መጋራት እንዲኖራቸው እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በሀገራቱ የሚገኙት የአቴከር ህዝቦች የጋራ ባህልን እና ቅርሶችን የሚጋሩ ሲሆን የውሃ እና ግጦሽ መሬት እጥረት ፈተናዎቻቸው እና የግጭት መንስኤ ሆነው ቆይተዋል።

በአብርሃም በለጠ
2023-01-02