
ዳግም በቻይና የተነሳውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ ሞሮኮ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ እገዳ ጣለች።
እገዳው ከጥር ሶስት ጀምሮ የሚደረግ ነው ያሉት የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚነሳበትን ቀን ወደፊት እናሳውቃለን ብለዋል።
ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ከቻይና ወደ ሃገራቸው የሚመጡ መንገደኞች የኮቪድ 19 ምርመራ ማድረግ ግዴታቸው መሆኑን የገለፁ ሃገራት መሆናቸውን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።
በማህሌት አማረ
2023-01-02