ሀገሬ ቲቪ

“2023 ለዓለም ኢኮኖሚ ፈታኝ ይሆናል” አይኤምኤፍ

የያዝነው ዓመት 2023 ለዓለም ኢኮኖሚ ፈታኝ እንደሚሆን የአይ ኤም ኤፍ ኃላፊ ክርስቲና ጆርጄቫ ገለጹ።

ኃላፊዋ የዓለምን ኢኮኖሚ በትልቁ ለሚያንቀሳቅሱት ለአሜሪካ፣ አውሮፓ እና ቻይና ኢኮኖሚ ዓመቱ ፈታኝ ይሆንባቸዋል ብለዋል።

የእነዚህ ሀገራት ኢኮኖሚ መቀዝቀዝ ማሳየቱ የዓለም ኢኮኖሚ በ2023 ይበልጥ አጣብቂኝ ውስጥ የመግባቱ ማሳያ እንደሆነም ጠቁመዋል ።

ይሄው ዓመት ካሳለፍነው የዩክሬን ጦርነት፣ የዋጋ ንረት እና ሌሎች ጉዳቶችን ካስተናገደው 2022 የበለጠ ፈታኝ ይሆናል ብለዋል።

በአብርሃም በለጠ
2023-01-02