በዘመናዊው ዓለም ውበት እና አለባበስ ተፈጥሮን ሲንተራሱ የበለጠ ውበታቸው ይጎላል። ይህንን ለማድረግ የተለይ እይታን እና ተሰጣኦን ሳይጠይቅ አይቀርም።
ለዚህ የታደለች ጃፓናዊት የ20 ዓመት ወጣት የበርካቶችን ቀልብ ያዝ ማድረግ ችላለች። ሞሞትሱኪ ላለፉት 14 ዓመታት በዚህ የፋሽን እና የጥበብ ስራ ውስጥ ቆይታለች።
ግዜ እና ለሙያው ያላት ፍቅር ቀስ በቀስ እየሞረዷት አሁን እጅን በዓፍ የምታስጭን ጥበበኛ ወትቷታል።
ፊውሪ ቀሚሶች በሚል መለያም የራሷን በአበቦች በመጠቀም የምታዘጋጃቸውን የቀሚስ ዲዛይን የያዙ ጌጣጌጦችን ለገበያ ታቀርባለች።
ለምናባዊ ፈጠራዎች የተለየ ፍቅር ያላት ይህችው ወጣት ዘወትር እነዚያን የምናብ ዓለም የተረት አልባሳት ወደ እውኑ ዓለም ለማምጣት ትጥር ነበር።
ኋላም አበቦችን በመጠቀም እነዚያን አልባሳት ዲዛይን ማድረግ እና ጌጣድርጋ መስራት እንደምትችል አመነች፤ ከዛም አደረገችው።
ከተፈጥሮ ጋር ልዩ ቁርኝት እንዳላት የምትናገረዋ ሞሞትሱኪ ከ14 ዓመት በፊት ስጀምረው ለኔ ከባድ ነበር ወደ ኋላ ግን ከስህተቶቼ እየተማርኩኝ በበርካታ የአበባ አይነቶች የልብስ ዲዛይን ያላቸውን ጌጦች መስራት ችያለሁ እላለች።
ይህችው ወጣት የምትሰራቸው ራዎች መነሻዎች ከእራሷ የግቢ ውስጥ የአበባ ስፍራ ነው። አንዳንድ ግዜ ግን በአካባቢዋ ያሉ ሰዎችን በማስፈቀድ ከአትክልት ስፍራቸው አበቦችን ትቀጥፋለች።
የመጀመሪያ ስራዋን ለገበያ ማቅረብ የቻለችው እንደ በ2013 ዓ.ም. ነበር። ታዲያ ከወራት በኋላ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ሳይቀር ስራዋ መሳብ መቻሉን ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል።
በሳምሶን ገድሉ
2023-01-02
