ሀገሬ ቲቪ

ትኩረት ያጣው በግንባታ ቦታዎች የሚደርስ አደጋ

የኮንስትራክሽን ባለሥልጣን በግንባታ ቦታዎች ላይ የሚደርሱ አደጋዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን እና የሚሰሩ የቁጥጥር ሥራዎችም ጠንካራ አለመኾናቸውን የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ጣሰው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ይህም በዘርፉ የሚደርሱ አደጋዎች እንዲበራከቱ ምክንያት ኾኗል ብለዋል።የኮንስትራክሽን ባለሥልጣን በዋናነት የፌደራል ተቋማት የሕንጻ ግባታዎች ላይ የደኅንነት ሥራዎች ስለመጠበቃቸው በቀጥታ ቁጥጥር ቢያደርም እዚያም ቢኾን ግን ችግሩ ከፍተኛ ነው ተብሏል።

የዘርፉ ተዋናይ ከኾኑ መካከል የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር በጉዳዩ ላይ ጠይቀናል።

በሀገሪቱ ያሉ የሕንጻ ተቋራጮች አቅም ደካማ መኾን እና የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ ያላደገ መኾኑ በግባታ ሠራተኛው ላይ አደጋዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት እንደኾኑ የማኀበሩ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ግርማ ሀብተማርያም ተናግረዋል።

ከዕለት ወደ ዕለት በዘርፉ በሚደርሱ አደጋዎች ሕይወታቸው የሚያልፍ ሠራተኞች ቁጥር በመበርከቱ የኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ከዓለም ባንክ በገኘው ድጋፍእየሰራሁት ያለው የሕግ ማዕቀ አለ ብሎናል።

ይህ እየረቀቀ ያለ ደንብ ውስከ 2016 ዓ.ም ጸድቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ሰምተናል። ረቂቅ ደንቡ ከበፊቶቹ የግንባታ ደኀንነት ላይ ከሰፈሩ ደንቦች የተሻለ እና ችግሩን የሚቀርፍ ነው ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-03