በአሸባሪነት የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂ ሃይል የመደምሰስ ዘመቻ አካል በሆነው በደቡብ ኦሮሚያና አዋሳኝ አካባቢዎች የተሰማራው ጥምር ጦር በሸኔ ይዞታ ስር የነበሩ በርካታ ቀበሌዎችን ማስለቀቅ መቻሉ ተነገረ።
በደቡብ ኦሮሚያ በሚገኙ ምዕራብና ምስራቅ ጉጅ እንዲሁም ቦረና ዞኖችን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ጥምር ጦር ስኬታማ ተልዕኮ ላይ ነው ተብሏል።
በዚህም ጥምር ጦሩ ባደረጋቸው የተጠኑ ዘመቻዎች ለዓመታት በሸኔ ይዞታ ስር የነበሩ ሰባት ቀበሌዎች ነፃ መሆናቸዉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።
በሙሉጌታ በላይ
2023-01-03
