ሀገሬ ቲቪ

ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ልትቀንስ ነው

የኬንያው ፕሬዝዳንት በሶስት ወር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ለማቅለል መንግስታቸው እየሰራ መሆኑን ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ዊልያም ሩቶ መንግስታቸው በሶስት ወራት ውስጥ ዝቅተኛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያ ተግባራዊ ለማድረግ በመስራት ላይ ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ መንግስታቸው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና ለአምራቾች ትኩረት አድርገን የታሪፍ ክለሳውን እናደርጋለን ብለዋል።

በነዚህ ወራት ውስጥ ለዝቅተኛው ማህበረሰብ መከፈል የሚችል ታሪፍን ለማዘጋጀት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።ሩቶ መግስታቸው የሀገሪቱን የብድር ጫና ለማቅለል እና የአየር ንብረት ለውጡን ጉዳት ለመቀነስም እንሰራለን ብለዋል።

በአብርሃም በለጠ
2023-01-03