ሀገሬ ቲቪ

በቡሩርንዲ የኮሌራ ወረርሺኝ መከሰቱ ተገለጸ

የቡሩርንዲ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር በዋና ከተማዋ ቡጁምብራ የኮሌራ ወረርሺኝ መከሰቱን አስታወቀ ።

በቡሩንዲ ብሔራዊ የህዝብ ጤና ኢንስቲትዩት ከቀናት በፊት በተደረጉ ምርመራዎች ላይ የኮሌራ ወረርሺ መከሰቱን አመላካች ውጤቶች ተገኝተዋል ተብሏል።

በምርመራ የተገኙት ኬዞች በሰሜናዊ ቡጂምቡራ ቡኪራሳዚ እና ሙታኩራ አከባቢዎች መሆነም ተገልጿል ።

የቡሩንዲ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሲልቪ ንዘይማና እንዳስታወቁት ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች በኮሌራ በሽታ መያዛቸው ታወቋል ብለዋል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-03