ሩሲያ የተራዘመ የድሮን ጥቃት ለመጀመር አቅዳለች ስትል ዩክሬን ከሰሰች።
ኢራን ሰራሽ የኾነ የሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ድሮን በመጠቀም ሩሲያ አዲስ ጥቃት ለመሰንዘር ማቀዷን ከደኀንነት ሪፖርት ማረጋገጣቸውን የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል።
ይህ የተገለጸው ዩክሬን በዶንባስ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ የሩሲያ ወታደሮችን እንደገደለች ካስታወቀች በኋላ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በተራዘመ የድሮን ጥቃት ዩክሬን ለማዳከም ሩሲያ አቅዳለች ስትል ነው እየከሰሰች ያለችው።
በሙሉጌታ በላይ
2023-01-03
