ሀገሬ ቲቪ

9ሺህ ኪሎሜትር በሳይክል የተጓዙት አባት እና ልጅ

በትምህርት ቤት እንደሁም በአካባቢዎ የአብራኮ ክፋይ በሆነው ልጆዎ ሰወች ሲማረሩ ሰምተው ያውቃሉ? ስሞታዎች ደርሶት ከሆነስ ውስኔዎ ምን ነበር?

ዛሬ በልጁ አስቸጋሪ ጸባይ መምህራኖቹ እንዲሁም የአካባቢው ሰወች ተማረው አይኑን እንዳናይ ያሉት አባት ልጁን ለመገሰጽ የወሰነውን አስገራሚ ውሳኔ እንንገሮ ።

አስቸጋሪና ከማህበረሰቡ ወጣ ያለ ጸባይ ያለውን ልጅ ይህ ጸባዩ እንዳያድግበት መቆጣት ሻገር ሲልም መምታት በኛ ኢትዮጵያዊያን የተለመደ ባህል ነው ።

ቻይናዊው አባትም በልጁ ላይ ተደጋጋሚ ስሞታ በሰማ ቁጥር ጸባዩን ካላስተካከለ የሚወስነው ውሳኔ ከ አቅሙ በላይ ሊሆን እንደሚችል ሲያስጠነቅቀው ቆይቷል ።

እንደ ዕድል ሆኖ ልጹ አስቸጋሪነቱን ማቆም አልቻለም አባትም ለሱም ለ 15 ዓመት ልጁም ከባድ የተባለውን ውሳኔ ውሰነ ። 9000 ኪሎ ሜትሮችን በብስክሌት ማቋረጥ ።

ለውሳኔው የሚሆነውን ቁሳቁሶች እንዲሁም ቀለብ በሚገባ ካዘጋጀ በኋላ ልጁን ከትምህርት ቤቱ በማስቀረጥ ጉዞ ይጀምራሉ።

ውሳኔው የተወሰነው አንድም በሚወጣቸው ዳገቶች ተፈትኖ ከዚህ በኋላ አይለመደኝም እንዲል አንድም ደግሞ ከአባትየው ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲጠናከር መሆኑን ተናግሯል ።

በጉዞ የተዳከመው ልጅ እባክህ ማረኝ ቢልም የአባት መልስ ግን ካሰብንበት ሳንደረስ ወድኋላ መመለስ የለም ሆኗል ።

በብስክሌታቸው የያዙትን ቀለብ እየቀመሱ እንዲሁም በመሸበት ድንኳናቸውን ዘርግተው በመተኛት 7 ወራትን የፈጀ 9 ሺ ኪሎ ሜትር ጉዞ ተጠናቀቀ ።

ልጅም ያን ጸባዩን ላይደግም ቃል ገባ አባትም ይህ ጉዞ ልጄ ያለውን ድብቅ ችሎታወች እንዳውቅ ረድቶኛልና በውሳኔዬ ደስተኛ ነኝ ብሏል።

እንዲ ያለ ቅጣት ተገቢ ባይሆንም ልጆችን ከመምታት ባሻገር አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ያልተገቡ ባህሪዎችን ማስተካክል እንደሚቻል የዚህ ግለሰብ ታሪክ ማስተማሪያ ነው።

በዮሴፍ ከበደ
2023-01-03