የገንዘብ ሚንስትር ከ43 ሚሊዮን ሊትር በላይ የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን አስታወቀ።
ሚንስትር መስሪያ ቤቱ በጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ ካምፓኒ የ43 ሚሊዮን 37 ሺ 412 ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ ነው የፈፀመው።
የምግብ ዘይቱ በአዲስ አበባ ባለ 3 ሊትር በ314 ብር፣ ባለ 5 ሊትር በ510 ብር እንዲሁም ባለ 20 ሊትሩ በ2003 ብር ለህብረተሰቡ የሚከፋፈል መሆኑን ጨምሮ አስታውቋል።
ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ አካባቢዎች የተወሰነ የትራንስፖርት ወጪን በመጨመር ለህብረተሰቡ ይደርሷል ብሏልመረጃውን ከገንዘብ ሚንስትር የማህበራዊ ገፅ አግኝተነዋል።
በሳምሶን ገድሉ
2023-01-03
