ወትሮም ሰላም የሚረቀው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዳግም ወደ ለመደው የግጭት አዙሪት ውስጥ እንዳይመለስ ተሰግቷል ።
ከቀናት በፊት በእስራኤል የተመሰረተው ጥምር መንግስት አክራሪ ብሄረተኞችና የይሁዲ እምነት ተከታዮች የበዙበት መሆኑ በቀጠናው ለሚገኙ ሃገራት ሰጋትን ጭሯል ።
ከቀጠናው ባሻገር ዋነኛዋ የጉዳዩ ባለቤት ፍልስጤም ደግሞ የተመሰረተውን መንግስት በይበልጥ በስጋትነት ተመለክታዋለች ።
በእስራኤል የተመሰረተው መንግስት ስራው አሃዱ ሲል የእስራኤል የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ሹም ኢታማር ቤን ጋቪር ለመጅመሪያ ግዜ በምስራቃዊ ኢየሩሳሌም የሚገኘውን አል-አቅሳ መስጊድን በከፍተኛ ጥበቃ ወስጥ ሆነው ሲጎበኙ ታይተዋል ።
ይህን ጉብኝት ተከተሎ በቀጠናው ስጋት ነግሷል ። የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ በበኩሉ ድርጊቱ ቀይ መስመር የጣሰ ነው ሲል አስጠንቅቋል ።
ቤን-ጋቪር በበኩላቸው መንግስታችን ለሃማስ ዛቻ እጅ አይሰጥም" ሲሉ በቃል አቀባያቸው በኩል ተናግረዋል።
ጉዳዩን እየተከታተለው ነው ያሉት የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽንፈኛው ሚኒስትር ቤን ጋቪር በአል-አቅሳ መስጊድ ያደረጉትን ጉብኝት አጥብቆ እንደሚያወግዝ እና ይህ ጉብኝት በእስራኤል ፍልስጤም ግጭት ላይ ቤንዝን እንደማርከፈከፍ ሊሆን ይችላል ብለዋል።
የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስቴር እና የተፎካካሪ ፓርቲው መሪ ያኢር ላፒድ በበኩላቸው የቤን ጋቪር ጉብኝት ለግጭት አባባሽ ሲሉ ጠርተወታል ።
ቤንጋቪር በንግግራቸው ይህ ቦታ ለእስራኤል ህዝብ በጣም አስፈላጊው ቦታ ነው, በዚህ ቦታ የሙስሊሞች እና የክርስቲያኖች የመንቀሳቀስ ነጻነትን እናስከብራለን ነገር ግን አይሁዶች ወደ እዚህ ሲመጡ ዛቻ እና ትንኮሳ በሚያደርጉ አካላት ላይ ህግ እናስከብራለን በለዋል ።
በፈንጆች አቆጣጠር በ2021 ለአስረ አንድ ቀን በጋዛ ቀጠና ተከስቶ ለነበረው የእስራኤል ፍልስጤም ግጭት በአል አሳቅ መስጊድ ውስጥ ተከስቶ የነበረው ግርግር ምክንያት መሆኑ ይታወሳል ።
ተከስቶ በነበረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እና በደርዘን የሚቆጠሩ የእስራኤል የፖሊሶች ለጉዳት እንዲዳረጉ ምክንያት ነበር ።
በእስራኤል በተካለለችው ምስራቃዊ እየሩሳሌም ውስጥ የሚገኘው ይህ መስኪድ የሚተዳደረው በዋክፍ እስላማዊ ጉዳዮች ምክር ቤት ቢሆንም እስራኤላዊያን ግን አሁን ላይ እየተጠቆጣሩት ይገኛሉ ።
ግጭት የማያጣው የእስራኤል ፍልስጤም ጉዳይ ይህን ምክንያት አግኝቶ ወዴት ያመራ ይሆን ግዜ ሚመልሰው ጉዳይ ነው።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-03
