ሀገሬ ቲቪ

በዕድሳት ላይ የሚገኘው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

የ 80 ዓመታትን ያስቆተረው የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ እየተከናወለት ይገኛል።

ካቴድራሉ መሰረታዊ የሚባሉ የእድሳት ሥራዎች ሳይሰሩለት በመቆየቱ የተነሳ ለከፋ ጉዳት መዳረጉን እድሳቱን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የካቴድራሉ አስተዳድሪ ሊቀ ስልጣናት ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ ተናግረዋል።

የካቴድራሉ አስተዳደር ከቅዱስ ሲኖዶስ ባገኘው ይሁንታ ከፌደራል ቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የጉዳቱን ጥልቀት የማስጠናት ሥራ እንዲሰራ በማድረግ እና ለእድሳቱ ስራ ጨረታ በማውጣት እና ውል በማሰር ወደ ማደስ ስራ መስራት መገባቱን ገልጸዋል።

ለሕንፃው እድሳትም 172 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግ ሰምተናል። ሕብረተሰቡም ለዚህ የሀገር ቅርስ የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪም ቀርቧል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-01-10