ዓለም የአየር ንብረት ለውጥ በሕዝቦች ላይ እያመጣ የሚገኘው ተጸኖ ለመቀነስ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ፊቷን አዙራለች።
በተለይም ከ መኪና የሚወጣው በካይ ጭስን ለመከላለከል በኤሌትሪክ እና በጸሃይ የሚሰሩ መኪናዎች በመተካት ተጸኖውን ለመቀነ እየተሰራም ዪገኛል ።
ከሰሞኑ ታዲያ በአውስትራሊያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ ቻርጅ 1000 ኪ.ሜ የሚጓዝ መኪና መስራታቸውን ይፋ አድርገዋል ።
በጸሃይ ቻርጅ የሚሰራው ይህ መኪና ያለ ማቋረጥ ለ12 ሰአት መጓዝ ይችላል ተብሏል ።ስዊፍት 7 የሚል መጠሪያ የተሰጠው መኪናው በኒው ሳውዝ ዌልስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራ ሲሆን መኪናው አዲስ የዓለም ክብረወሰን መስበሩም ተነግሯል።
መኪናው በሰዓት 85 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችል ሲሆን፤ ይህም በአንድ ጊዜ ቻርጅ ከ1000 ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ የቻለ ፈጣኑ የኤሌክትሪክ መኪና አስብሎታል።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሰሩት መኪና ፍጥነቱ እና ብቃቱ ከተረጋገጠ በኋላ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ እንደሚሰፍርም ተነግሯል።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-10
