ሀገሬ ቲቪ

የባይደን ቢሮ ውስጥ የተገኙት ሚስጢራዊ ሰነዶች

የዓለምን ኢኮኖሚ በእጆቿ የምትዘውረው ሀገረ አሜሪካ የሚያስተዳድሯት መሪዎቿ በየጊዜው በርካታ ሚስጢራዊ ስራዎች እንደሚሰሩ ጊዜ ቀስ በቀስ እያጋለጣቸው የመጣ ይመስላል።

በአሜሪካን የመሪዎች ታሪክ ውስጥ አርባ ስድስተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ፕሬዝዳት ጆ ባይደን የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ምክትል ሁነው ሃገሪቱን ሲያስተዳድሩ በነበሩበት ጊዜ ጅምሮ በቢሯቸው የተቀመጡ ሚስጢራዊ ሰነዶች ላይ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የሃገሪቱ የፍትህ ቢሮ ይፋ አድርጓል።

ሚስጢራዊ ሰነዶቹም የግል ጠበቆቻቸው በፔንሲልቫንያ ዩንቭርሲቲ የሚገኘውን የባይደን የዲፕሎማሲ ቢሯቸውን በሚዘጉበት ጊዜ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

ጠበቆቹም ያገኟቸውን ሚስጢራዊ ሰነዶች በቀጥታ ወደ ብሄራዊ ቤተ መዛግብት ልከዋቸዋል።

የአሜሪካ የፍትህ ቢሮ በባይደን የቀድሞ ቢሮ ውስጥ የተገኙትን አስር ሚስጢራዊ ሰነዶች ወደ ፖሊሲ ምርምር ኢኒስቲቲውት ተልከው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው፡፡

የጠቅላይ አቃቤ ሕግ መሪክ ጋርላንድ ከኤፍ ቢ አይ ጎን ለጎን ምርመራውን በበላይነት እንዲመሩት ጠበቃ ጆን ላውሽ ይመሩታል ብለዋል።

በባይደን የቀድሞ ቢሯቸውኦውስጥ ሚስጥራዊ ሰነዶች መገኘት ዜና ይፋ ከሆነ በኋላ በአወዛጋቢነታቸው የሚታወቁት እና ተቀናቃኛቸው ትራንፕ በማህበራዊ ገፃቸው ኤፍ ቢ አይ በሌሎች የባይደን ቤቶች ነጩን ቤተ መንግስት ጨምሮ መቼ ነው ምርመራ የሚያደርግባቸው ሲሉ ፀፈዋል።

ትራንፕ ከስልጣናቸው ከወረዱ በሁኋላ ወደ 300 የሚጠጉ ድብቅ ሰነዶችን ወደ ፍሎሪዳ ወስደዋል። እነዚህን ሰነዶች እንዲመልሱ በቀረበባቸው ክስ ተቃውመው እየተከራከሩ ይገኛሉ።

የጆ ባይደን ሰነዶች ሁኔታም ከትራምፕ ከተያዙ ሰነዶች ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ የተለየ ነው።

ጆ ባይደን በግሉ እና ሆን ብሎ የተደበቁ ቁሳቁሶችን የያዘ አይደለም ለመንግስትም ለመመልስ ምንም አይነት ተቃውሞም ተላቸውም ሲል ዘጋርዲያን ዘግቧል።

የባይደን ፋይሎች የተገኙት የፍትሕ ሚኒስቴር በጎልፍ ክበቡ ውስጥ በተገኙት ፋይሎች ላይ ትራምፕን በወንጀል ለመወንጀል ወይም ላለመወንጀል የሚወስን ነፃ ጠበቃ እንደሚሾም ከማሳወቁ ከጥቂት ጊዜ በፊት ነበር።

ይህም ታዲያ የፍትህ ቢሮውን አጣብቂኝ ውስጥ ያስገባዋል ተብሏል።

በማህሌት አማረ
2023-01-10