ሀገሬ ቲቪ

ለፓኪስታን ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊደረግ ነው

በጄኔቫ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ የተሳተፉ ሀገራት ለፓኪስታን የ9 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ።ፓኪስታን በ2021 አጋጥሟት ከነበረው ከባድ የጎርፍ አደጋ ለማገገሚያ ድጋፉን ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ፓኪስታን ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ ለማግኘት በጄኔቫ ጉባኤ አካሂዳለች።

ለማገገም ያስፈልገኛል ካለችው የ16.3 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ገንዘብ ግማሽ ያክሉን ድጋፍ ሊያደርጉላት ተስማማተዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-10