ሀገሬ ቲቪ

ሩዋንዳ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሰደተኞችን አልቀበል አለች

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚነሱ ስደተኞችን መቀበል አንችልም ብለዋል።

በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚገኘው የማአድን ሰፍራን ለመቆጣጠር በኤም 23 አምጺያን እና በመንግስት ሃይሎች መሀከል በሚካሄደው ጦርነት ላይ ሩዋንዳ አምጺያኑን ትደገፋለች ስትል ኮንጎ በተደጋጋሚ ትከሳለች።

ሩዋንዳ በበኩሏ በጦርነቱ ጣልቃ እንዳልገባች ተናግራለች። ይህን ወንጀላ ተከትሎ ሩዋንዳ ከኮንጎ ምንም አይነት ስደተኛ እንደማትቀበል አስትወቃለች።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሪፖርት እንድሚያሳየው እስከ ህዳር 2022 ድረስ ከ 72 ሺ የሚበልጡ ስደተኞች በሩዋንዳ እንደነብሩ አመልክቷል ።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-10