ሀገሬ ቲቪ

የቀድሞ የብሔራዊ የመረጃ ደህንነት ም/ዋና ዳይሬክተር ከእስር ተለቀቁ

በአቶ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ ስር ጉዳያቸው በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲታይ የነበሩ ዘጠኝ ተከሳሾች ከእስር ተለቀቁ።

የቀድሞ የብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ዘሪሁንን ጨምሮ ዘጠኝ ተከሳሾች ናቸው ከእስር የተፈቱት።

ተከሳሾቹ ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት ከአራት ወር እስር እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የነበረ ሲሆን ፤ 3ቱ የእስር ጊዜያቸውን ሲያጠናቀቁ የተቀሩት ሰባቱ በአመክሮ እንደተፈቱ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት ከእስር የተፈቱት ተከሳሾች ቀደም ሲል በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ ሲሆን ፣ በኋላ ላይ ጉዳያቸው ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ጋር እንደተያያዘ ይታወሳል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-10