ሀገሬ ቲቪ

የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ገቡ

አዱሱ የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የመጀመሪያ የጉብኝት መዳረሻቸው ኢትዮጵያ ኾናለች።

ሚንስትሩ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቺን ጋንግ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በግብጽ፣ ጋቦን፣ አንጎላ እና ቤኒን ጉብኝት ያደርጋሉም ተብሏል።

በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ኀብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ይወያያሉም ተብሏል።

ቺን ጋንግ በአፍሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት የቻይና አፍሪካ ወዳጅነትን የበለጠ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-10