ሀገሬ ቲቪ

የህውሓት ከባድ መሳሪያዎችን ማስረከብ ጀምሯል

የህውሓት ኃይሎች በስምምነቱ መሠረት ከባድ መሳሪያዎችን እና ትጥቆችን እያስረከቡ ነው ተባለ።

በአፍሪካ ኀብረት አደራዳሪነት በፌደራል መንግሥቱ እና በህውሓት መካከል ከተደረገው ስምምነት አንዱ የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎችን ህውሓት ለፌደራል መንግሥቱ ማስረከብን ይጨምራል።

በዚህ ስምምነት መሠረት ቡድኑ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እያስረከበ መኾኑ ተሰምቷል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-11