በሰሜኑ የኢትዮጲያ ክፍል በነበረው ጦርነት ሳቢያ በርካታ የጤና ተቋማት ለውድመት ተዳርገዋል።
ውድመት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማትን መልሶ ወደ ስራ ለማስገባት 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብር እንደሚያስፈልግ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የጤና ሚኒስቴር አጋር አካላትን በማስተባበር በአማራ ክልል 40 ስሆስፒታሎች እና 415 የጤና ጣቢያዎች፤ በአፋር አንድ ሆስፒታል እና ሃያ የጤና ጣቢያዎች፤ በትግራይ በሶስት ከተሞች 12 ሆስፒታሎች እና 28 የጤና ጣቢያዎች በከፊል ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ተገልጿል።
በማህሌት አማረ
2023-01-11
